ዜና | Oduu | News
ባለፉት 6 ወራት ተግባራትን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በመከወን ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገቡን የልደታክ/ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት ገለፀ።

ጽ/ቤት የ6ወር የእቅድ አፈፃፀም እና የተከለሰ የቀሪ 6 ወራት እቅድ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል ። በውይይቱ ወቅት የጽ/ቤቱ ሀላፊ ኢንጅነር ቅድስት ማቲዎስ እንደገለፁት ባለፉት 6 ወራት ስታንዳርዳቸውን የጠበቁ የመንግስት ህንፃዎችን በማልማት ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር እና የማስተዳደር ስራ መሰራት መቻሉን ገልፀዋል። ኃላፊዋ አክለውም ምቹ የስራ አካባቢ የፈጠሩ የመንግስት ተቋማትን በማሳደግ የዘመነና ከብክነት የፀዳ የመንግስት ንብረት አስተዳደር መፍጠር መቻሉንም ገልፀዋል። ውስን የሆነውን የህዝብ እና የመንግስት ሀብት ለታለመለት አላማ እንዲውል ለማስቻል እና የህንፃ አገልግሎት ስርአትን በማሻሻል ቀልጣፋ እና ውጤታማ የመረጃ አያያዝ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአት እንዲኖር ለማስቻል እየተሰራ ነው ብለዋል ኢንጅነር ቅድስት። በቀጣይ 6 ወራት ቀሪ እቅድን ለመፈፀም በተሻለ የስራ ተነሳሽነት የተቀመጡ ግቦችን ማሳካት ይገባል ብለዋል። የውይይቱም ተሳታፊዎች እንደገለፁት ፅ/ቤቱ ውስን የሆነውን ሀብት ከብክነት አድኖ ለታለመለት አላማ እንዲውልና ምቹ የስራ አካባቢ በመፍጠር ረገድ የሰራው ስራ የተሻለ መሆኑን ገልፀዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን ጠግኖ በመጠቀም ከትርፍ ወጪና የሀብት ብክነት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።

የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት "መልሶ ጠግኖ የመጠቀም ባህል ለከተማችን ሁለንተናዊ ብልፅግና "በሚል መሪ ሃሳብ ከወረዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ከጤና ጣቢያና ከትምህር ቤት ተቋማት ከክፍለ ከተማ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄዷል። የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ማቲዎስ እንደገለፁት መጠገን የሚችሉ የመንግስት ንብረቶችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም ከትርፍ ወጪና የሀብት ብክነትን በጋራ በመስራት መከላከል እንደሚገባ ገልፀዋል። የኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸሮችን ጠግኖ በመጠቀም ትርፍ ወጪና የሀብት ብክነት ለመቀነስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የገለፁት ወ/ሮ ቅድስት አያይዘው በቀጣይ በምንሰራቸው ተግባራት ውጤታማ ለመሆን ሁሉም ተጠሪ ተቋማት ሚናቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አበራ ተስፋዬ በመድረኩ እንደተናገሩት የመንግስትን ንብረት መልሶ ጠግኖ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀው ሃብትን ከብክነት ለመከላከል የሁሉም ዜጋ ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀዋል። የመንግስት ንብረትን ጠግኖ መልሶ ጥቅም እንዲውሉ ማድረግ ተገቢና መንግስት ያለ አግባብ የሚያወጣውን ወጪ በማስቀረት ይገባል ያሉት አቶ አበራ ተስፋዬ አያይዘው በየተቋሙ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል ሲሉ ገልፀዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎችም ተቋማት በቅንጅት በመስራት የተጎዱ የመንግስት ንብረቶችን ጠግኖ መልሶ በመጠቀም የመንግስት ወጭን ማዳን እንደሚገባ አንስተዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ገመገመ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ቅድስት ማቴወስ እንደተናገሩት ተቋማትንና ንብረትን በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያስችሉ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑንና የተቋማትን ንብረቶች እርጅና ቅናሽ በመስራት ንብረቶች በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲወሉ እየተደረገ ይገኛል። ወ/ሮ ቅድስት አክለውም በ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት በጤና ተቋማት፣በትምህርት ቤቶችና በወረዳዎች እንዲሁም በክፍለ ከተማ ተቋማት ላይ ያሉትን ንብረቶች መረጃ በአግባቡ በማደራጀት ለቁጥጥር አመቺ እንዲሆኑ መሠራቱን ገልጸው በቀጣይም በአፈጻጸማችን ላይ የነበሩትን ጥንካሬዎች በማስቀጠል የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ በመተባበር ልንሰራ የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የህንጻዎችንና ሌሎች ንብረቶች አገልግሎት ላይ መዋል ሲጀምሩ ያላቸውን ዋጋ መግለጽና እርጅና ቅናሽ መስራት የሚገባ መሆኑን ገልጸው ይህ መሆኑ የመንግስትን ንብረት በአግባቡ ለመያዝና ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል አሰራርን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል።

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
በመልካም አስተዳደር የ2ኛ ሩብ አመት ድጋፍና ክትትል እንዲሁም በንብረት አስተዳደር ኦን ላይን ምዝገባና በስተታንዳርድ የሞዴል ተቋም ፈጠራ ላይ ውይይት ተደረገ።

በመድረኩ በቅንጅታዊ አሰራር በተደረገ ክትትልና ድጋፍ የተገኙ ግኝቶች የጋራ ተገርጓል ። የልደታ ክፍለ ከተማ አ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ እንዳሉት የመልካም አስተዳደርና በተያዘው መፍታት ይገባል በማለት የተያዘውን እቅድ በትኩረት መፈፀም እንደሚገባ ገልፀዋል። የመልካም አስተዳደር ችግሮች በተያዘው ጊዜ በመፍታት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል ያሉት አቶ ጢቂ አያይዘው ጽ/ቤቶችን ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ ይጠይቃል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የመልካም አስተዳደር ቅሬታና አቤቱታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ይልማ ተረፈ እንደተናገሩት የመንግስት ትልቅ የትኩረት አቅጣጫ የሆነውን የመልካም አስተዳደር ማስፈን ቅሬታን መቀነስ መሆኑን በመያዝ ተከቢውን ስራ በቅነንጅት መርራት ይገባል በማለት ገልፀዋል። ቅንጅታዊ አሰራር ላይ በጋራ እየተሰራ ያለበት አገራት ባብ የተሻለ ውጤት እያመጣ ነው ያሉት አቶ ይልማ መልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሁንም በትኩረት መስራት ይገባል በማለት ገልፀዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር ሀላፊ ወ/ሮ ቅድስት ማቴዮስ እንዳሉት ተቋማትን ለአገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስታንዳርዱን የጠበቀ በማድረግ ለተገልጋዩ ቋሚና የስቶክ ንብረቶችን ወደ ሲስተም በማስገባት መሄድ ይገባል ያሉት ወ/ሮ ቅድስት አያይዘው ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል

image
image
image
image
ዜና | Oduu | News
ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ።

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በቀጣይ 10 ቀናት የሚተገበሩ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ላይ የክ/ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት ውይይት በማካሄድ አቅጣጫ ተቀመጠ። የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጢቂ ድሪባ በመድረኩ ላይ እንዳሉት የህዝብንና የመንግስትን ሀላፊነት በጊዜ የለኝም መንፈስ በመስራት ከተማችን እንዲሁም ክ/ከተማው የያዙትን የልማት እና መልካም አስተዳደር ቁልፍ ተግባራት በቁርጠኝነት በማስፈፀምና በመፈፀም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣይ ይገባል ብለዋል። አቶ ጢቂ አያይዘው ለቀጣይ ተልዕኮ የሚመጥን የአመራር ቁመና በመላበስ የልደታን ከፍታ ለማረጋገጥ የመንግስትና የፓርቲ ተግባራትን በትጋት፣ በቁርጠኝነት፣ በውጤት እና በስነ-ምግባር መምራት እንደሚገባ አሳስበዋል። ይህ አመራር የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደሩ ከተያዙ ስትራቴጂክ ግቦች የተቀዱ የ10 ቀናት ተግባራትን መፈፀምና ማስፈፀም የሚችል የማህበረሰቡን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የሆነ፤ የሚሰጠውን ተልዕኮ አቀናጅቶ መምራትና ሀላፊነቱ በአግባቡ መወጣት የሚችል መሆን አለበት በመድረኩ አቅጣጫ ተቀምጧል። በመድረኩ ዋነኛ የትኩረት መስክ የሆኑት ሰዉ ተኮር ተግባራት፣ የፀጥታ፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የሌማት ትሩፋት እና የኢንሼቲቭ ስራዎችን ሌሎች የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

image
image
image
image