የልደታ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት በአዋጅ ቁ. 90/2017 መሠረት የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል

  1. በመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ላይ ለክ/ከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ ያማክራል፤
  2. ስልጣኑ በህግ ለሌላ አካል ወይም ለሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ካልተሰጠ በቀር የክ/ከተማዉን አስተዳደር ህንፃዎችንና ቋሚ ንብረቶችን ይመዘግባል፤ በበላይነት ያስተዳድራል፤ ያድሳል፤ ጥገና የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች በመለየት እንዲጠገን ያደርጋል፤
  3. የህንጻና ንብረት አስተዳደር እና አጠቃቀም ዘመናዊ ስርዓትን ይዘረጋል፤ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፤ ምድረ ግቢን ውብና ማራኪ እንዲሆኑ ያደርጋል፤
  4. የመንግስት ህንፃዎች አጠቃቀም፣ ለተጠቃሚው ያላቸው ተደራሽነት እና ከወጪ አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤
  5. የክ/ከተማዉን አስተዳደሩ የመንግስት ተቋማት ለአገልገሎት አሰጣጥ የሚያስፈልጋቸውን ህንፃዎች የኪራይ ደረጃ አጥንቶ ይወስናል፤ ለመንግስት አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች እንዲገነቡ ያደርጋል፤
  6. በክ/ከተማዉን ውስጥ ባለቤት የሌላቸው ህንጻና ንብረቶችን አግባብ ባለው ህግ መሰረት ተረክቦ ያስተዳድራል፤
  7. የመንግስት ህንፃዎች ወጥ የሆነ ስታንዳርድ እና ዲዛይን እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ይሰራል፤ ያስገነባል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
  8. የህንጻ አስተዳደር ሥራዎች የተቀላጠፉና ውጤታማ እንዲሆኑ የውስጥ አደረጃጀት እና የቢሮ ቁሳቁስ ስታንዳርድ ያዘጋጃል፤ እንዲተገበር ያደርጋል፤
  9. በመንግስት የንብረት አያያዝ ስርዓት መሰረት የመንግስት ንብረቶች በአግባቡ ስለመያዛቸው እና ጥቅም ላይ ስለመዋላቸው የንብረት ኦዲት ያደርጋል፤
  10. በጽ/ቤቱ የህንጻና የንብረት ኦዲት ውጤት መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ ያልወሰዱ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን ለይቶ ተጠሪ ለሆነለት ቢሮና ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤
  11. አግባብ ባለው ህግ ቋሚ ንብረቶች ዋጋ እንዲወጣላቸው እና በየዓመቱ የዕልቀት ዋጋ እንዲሰላላቸው በማድረግ መንግስት የቋሚ ንብረቶች የያዙትን ዋጋ እንዲያውቅ ያደርጋል፤
  12. በጽ/ቤቱ በሚያስተዳድራቸው ንብረቶች ላይ የሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ይከላከላል፤ ተፈጽሞም ሲገኝ ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል ወይም እንዲወሰድ ያደርጋል፤
  13. የመንግስት ህንፃዎች የሚገነቡበት ቦታ ያስፈቅዳል፤ ይመዘግባል፤ ተገቢውን የይዞታ ማረጋገጫ እና የግንባታ ፈቃድ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ይጠብቃል፤
  14. የመንግስት ህንፃዎች የሰራተኞች ካፍቴሪያ፣ የጽዳትና ውበት፣ የጥበቃ፣ የመጀመሪያ ህክምና፣ የመንግስት ተሸከርካሪዎች ማቆሚያ፣ የመኪና እጥበት እና የህፃናት ማቆያ አገልግሎቶች ተግባራትን ያከናውናል፡፡